Welcome to the Ethiopian Electric Utility Chatbot

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደንበኞቹን ፍላጎት ለማርካት የቴለግራም ቦት(@EeuchatBot) በመተግበር ደንበኞች የቆጣሪ ንባብ እራሳቸዉ ማስገባት የሚችሉበትን ሁኔታ አመቻችቷል። በመሆኑም ደንበኞች ከዚህ በታች በተገለጸዉ መልኩ የወርሃዊ የሀይል ፍጆታ ንባብ መላክ እንደሚችሉ እንገልጻለን።

በተሌግራም ቦቱ የሚያገኟቸዉ አገልግሎቶች የሚከተሉት ናቸው፦

ወርሀዊ የቆጣሪ ንባብዎን ለማስገባት እንዲችሉ @EeuchatBot የሚለዉን ይጫኑ

EEU
What can this bot do?
Dear customer, thank you for messaging with this Ethiopian
Electric Utility Chat bot. For messaging with us, this Ethiopian
can assist you with:
- Registering complaint:
- Checking your bill status
- Send Meter Reading
- Planned Interruption
To start the bot simply write /start
Dec 21
/start
7:52 PM ✓

ቴሌግራም ቦቱን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚጠቀሙ ከሆነ

/Start የሚለዉን ሲጫኑ ሁሉም አገልግሎቶች ለእርስዎ ክፍት ይሆናሉ።

የቆጣሪ ንባብ እንዴት ማስገባት ይችላሉ?

  1. ከተዘረዘሩት አገልግሎቶች መካከል Send Meter Reading የሚለዉን ይምረጡ
  2. Contract Account Number (CA-Number) ያስገቡ
  3. የቆጣሪ ንባብ መቀበያ ጊዜ ክፍት ከሆነ አሁን ያለዉን የቆጣሪዎን ንባብ / KWh reading ያስገቡ።
  4. ያስገቡት መረጃ ትክክል መሆኑን እንዲያረጋግጡ የእርስዎ አጠቃላይ መረጃ ዝርዝር ይመጣልዎታል።
  5. ያስገቡት መረጃ ትክክል ካልሆነ Cancel ብለዉ እንደገና ይጀምሩ። መረጃዎ ትክክል ከሆነ Send የሚለዉን ተጭነዉ ይጨርሱ።
ያስተዉሉ: አንዴ የቆጣሪ ንባብ መረጃዎን ከላኩ በኋላ ድጋሚ ማስተካከል አይችሉም። ድጋሚ ማስተካከል ቢፈልጉ የቆጣሪ ንባብ መረጃዎን(ለምሳሌ ፎቶ) ይዘው ወደ አግልግሎት ማዕከል በመሄድ ማስተካከል ይኖርብዎታል።
EEU
Please select the service you need from the options below
REPORT CORRUPTION
CHECK BILL
SEND METER READING
PLANNED INTERRUPTION
7:52 PM
SEND METER READING
6:43 PM
EEU
Enter your Contract Account Number(CA-Number)
6:43 PM
10000123456
6:43 PM

የኮንትራክት መለያ ቁጥርዎን ወይንም(CA-Number) ሲያስገቡ

ከቦቱ የሚከተሉትን መልዕክቶች ካገኙ ፥

EEU
! Your service center has not started accepting meter reading
submissions at this time. We apologize for any inconvenience and
will notify you once this feature becomes available.
1:32 PM

ይህ ማለት ይሄ አገልግሎት እርስዎ ለሚገኙበት አገልግሎት ማዕከል ክፍት አይደለም ማለት ነዉ። ስለዚህ ይህን አገልግሎት ለጊዜዉ መጠቀም አይችሉም።

የቆጣሪ ንባብ መቀበያ ወቅት ደርሶ ከሆነ

አሁን ያለዉን የቆጣሪ ንባብዎን / KWH reading እንዲያስገቡ ይጠየቃሉ፦

EEU
⏰ Previous Reading Date: 2025-10-25
⚡ Previous KWh reading: 3575
Enter your KWh reading. Please only write the digits.
2:24 PM
67834
2:24 PM

ቁጥሮች ብቻ ያስገቡ፣ ከነጥብ ቀጥሎ ያለውን ምንም አይነት አሃዝ አይጻፉ። ለምሳሌ የቆጣሪዎ ንባብ 67834.45 ከሆነ፣ ከነጥብ በፊት ያለዉን 67834 የሚለዉን ብቻ ይፃፉ።

የKWH ንባብዎን ሲያስገቡ፦

ያስገቡት የቆጣሪ ንባብ/KWH reading ከዚህ በፊት ከተመዘገበዉ ንባብ ያነሰ ከሆነ፣ ከዚህ በታች ያለዉን መልዕክት ያገኛሉ፦

3500
2:42 PM
EEU
! The meter reading you submitted — 3500.0 KWh is less than the previous reading — 3575 KWh.
Please ensure you entered a valid reading. If your meter has reversed, visit the Customer Service Center for further assistance.
2:42 PM
ማስታወሻ፦

ማጠቃለያ

KWH ንባብዎን እንዳስገቡ፣ ያስገቡት መረጃ ማጠቃለያ ይመጣልዎታል። ትክክለኛነቱን ለማረጋገጥ ሁሉንም ዝርዝሮች በጥንቃቄ ይፈትሹ። ትክክለኛ ሆኖ ካገኙት Send የሚለዉን በመንካት ንባብዎን ይላኩ ካልሆነም Cancel የሚለዉን በመንካት ያቋርጡ።

EEU
Please check your information
👤 Customer number: [XXXXXX]
⚡ Meter type: Single Phase
Please read and be sure of the information before submitting. Once you hit send, you won't be able to edit anything.
Choose action:
✓ Send
✗ Cancel
2:54 PM
ያስተዉሉ: አንዴ የቆጣሪ ንባብ መረጃዎን ከላኩ በኋላ ድጋሚ ማስተካከል አይችሉም። ድጋሚ ማስተካከል ቢፈልጉ የቆጣሪ ንባብ መረጃዎን(ለምሳሌ ፎቶ) ይዘው ወደ አግልግሎት ማዕከል በመሄድ ማስተካከል ይኖርብዎታል።

Send ሲጫኑ...

የሚከተሉትን መልዕክቶች ካገኙ የዚህ ወር የቆጣሪ ንባብዎ እኛ ጋር ደርሷል ማለት ነዉ፦

Send
3:04 PM
EEU
✓ Your Meter reading data is sent successfully
3:04 PM

ወይም ንባብዎ አስቀድሞ ተነቦ ወደ እኛ ሲስተም ተልኮ ከሆነ ይህን መልዕክት ያገኛሉ፦

EEU
✓ Meter submission has already been recorded for this customer. No further submission is needed at this time.
Customer: [XXXXXX]
Existing Reading: 6042 KWh
Reading Date: 2025-12-26
1:49 PM

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ቴሌግራም ቦትን ስለተጠቀሙ እናመሰግናለን !